ማርቲን ሉተር ኪንግ፣ ኃይል አልባ ትግል እና ተግባራዊ ተሞክሮዎች
በግሪጎሪያን የዘመን ቀመር መሰረት ከ2011 ጀምሮ፥ ዓለም በጥልቀት አወዛጋቢ ሆና ነው የቆየችው። ምንም እንኳን የትጥቅ ትግሎች በመካከለኛው ምስራቅ፥ የሳህል ቀጠናዎች እና ደቡብ እስያ ውስጥ ተቀስቅሰው የነበረ ቢሆንም፥ ብጥብጥ የተሞላባቸው የእርስበርስ ግጭቶች፣ ከእንግዲህ ወዲያ ሰዎች ለለብሶቶቻቸው መፍትሄ ለማግኘት የሚፈልጓቸው ተቀዳሚ መንገዶች አይደሉም። ይልቅስ፥ ከቱኒዝያ እስከ ጣህሪር አደባባይ፥ ከዙኮቲ ፓርክ እስከ ፈርግሰን፥ ከቡርኪና ፋሶ እስከ ሆንግ ኮንግ ድረስ… በዓለም ዙሪያ የተደረጉ ህዝባዊ ንቅናቄዎች፥ ከጋንዲ፣ ከማርቲን ሉተር ኪንግ እና ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አገራት ለውጥን ለማራመድ የተጠቀሟቸውን ልምዶችን መሰረት ያደረጉ ነበሩ።
Translated by Yohanes Molla and reviewed by Abebe Gellaw, March 2018